አፍሪካ መር የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔዎችን የያዘው “የአዲስ አበባ መግለጫ” ተግባራዊ እንዲሆን መንግስት ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ገለፁ፡
ከጳጉሜን 3 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተካሄደው 2ኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ የሀገራት መሪዎችን ጨምሮ ከ25 ሺህ በላይ ሰዎችን በማሳተፍ በስኬት ተጠናቋል።
ጉባኤው በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ ግለሰቦች እና ተቋማትም እውቅና ተሰጥቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤትን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት እና ግለሰቦች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ የተፈረመውና አፍሪካ መር የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔዎችን የያዘው “የአዲስ አበባ መግለጫ” ተግባራዊ እንዲሆን መንግስት ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል በተካሄደው ጉባኤ አፍሪካ በ30ኛው የዓለም አየር ንብረት ጉባኤ (COP30) ላይ መፍትሔ ተኮር ተሳትፎ የምታደርግበትን አቅጣጫ አስቀምጦ መጠናቀቁ ይታወሳል።
በካሳሁን አንዱአለም