በስሎቬኒያ ሉብሊያ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ ድል ተቀዳጁ

You are currently viewing በስሎቬኒያ ሉብሊያ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ ድል ተቀዳጁ

AMN ጥቅምት 9/2018 ዓ.ም

በሱሎቬኒያ ሉብሊያ በተካሄደ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ ድል ተቀዳጅተዋል።

በወንዶች ውድድር አትሌት ሃፍታሙ አባዲ በ2:06:52 በመግባት በቀዳሚነት አጠናቋል።

በውድድሩ ላይ የተሳተፈው ሌላኛዉ ኢትዮጵያዊ አትሌት ከማል ሁሴን ሦስተኛ ወጥቷል።

በሴቶች አትሌት ትግስት ገዛኸኝ በ2:22:46 በመግባት በአንደኝነት አሸንፋለች።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review