አባታችን የሁሉም ኢትዮጵያዊ አባት ነበሩ

You are currently viewing አባታችን የሁሉም ኢትዮጵያዊ አባት ነበሩ

AMN- ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም

አባታችን የሁሉም ኢትዮጵያዊ አባት ነበሩ ሲሉ የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ልጅ ተናገሩ፡፡

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ አስከሬን የሽኝት ሥነ- ሥርዓት በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

በሽኝት መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት ቤተሰቦቻቸው በልጃቸው አህመድ ኡመር አማካኝነት ባስተላለፉት መልእክት አባታችን የእኛ ብቻ አባት አይደሉም የሁሉም ኢትየጵያዊ አባት ናቸው ብለዋል።

በተለይ የኢትዮጵያ ህዝብ ያለምንም ልዩነት ላሳያቻው ክብር እና ፍቅር ምስጋና አቅርበዋል።

የአስከሬን ሽኝት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ተከናውኗል፡፡

በሽኝት ስነ-ስርአቱ የኢፌደሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴን ጨምሮ የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ፣ የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ኡለማዎች፣ ደረሳዎቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል ።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review