በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ8ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ዌስትሃም ዩናይትድ በሜዳው በብሬንትፎርድ 2ለ0 ተሸንፏል።
የኢጎር ቲያጎ እና ማቲያስ ያንሰን ግቦች ለብሬንትፎርድ ሙሉ ሦስት ነጥብ አስገኝተዋል።
ግርሃም ፖተርን አሰናብተው ኑኖ ስፕሪቶ ሳንቶን የቀጠሩት ዌስትሃሞች ውጤታቸው አልተሻሻለም።
ሦስት ጨዋታ የመሩት ኑኖ በሁለቱ ተሸንፈው በአንዱ አቻ ተለያይተዋል።
ዌስትሃም በአጠቃላይ በሊጉ ካደረጋቸው ስምንት ጨዋታዎች በስድስቱ ተሸንፏል።
በሸዋንግዛው ግርማ