ከባለድርሻ አካላት ጋር በተሰራ ስራ የደንብ መተላለፍ 83 ከመቶ ቀን ሷል፡- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን

You are currently viewing ከባለድርሻ አካላት ጋር በተሰራ ስራ የደንብ መተላለፍ 83 ከመቶ ቀን ሷል፡- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን

AMN – ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማ የደንብ ጥሰት የማይታይባት ከተማ ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት ለማሳካት ባለድርሻ ተቋማት በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጠይቋል፡፡

ባለስልጣኑ በ2018 በጀት ዓመት በአንደኛው ሩብ ዓመት ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር እየገመገመ ነው::

የባለስልጣኑ ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ የከተማዋን ደንብ መተላለፍ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ዉጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል::

በዚህም ባለስልጣኑ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በሰራቸው ስራዎች የደንብ መተላለፍን 83 ከመቶ መቀንሱን ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል::

ለከተማዋ ሁለተናዊ ዕድገት ደንብ መተላለፍ የማይፈጠርባት ከተማ ለማድረግም የተጀመሩ ተግባራትን በትብብር መስራት ይገባል ሲሉም ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አስገንዝበዋል፡፡

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review