ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በማበርከት የአመቱ ልዩ ተሸላሚ ሆነ

You are currently viewing ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በማበርከት የአመቱ ልዩ ተሸላሚ ሆነ

AMN ጥቅምት 11/2018

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት አመት በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የእዉቅና እና የሽልማት መርኃ ግብር አካሂዷል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻን ጨምሮ ከፍተኛ የካቢኔ አባላት፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በመስጠት አያጎልም የበጎ ፍቃደኞች እውቅና መርሀ ግብር በ2017 በጀት አመት በነበረው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ 1 ሚሊየን እስከ 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ድረስ አስተዋጽኦ ላበረከቱ 4 መቶ 83 ለግል ፤ ለመንግስት ተቋማትና ባለሀብቶች እውቅና ሰጥቷቸዋል፡፡

የአቅመ ደካሞችና የሀገር ባለውለታዎችን ቤት በማደስና በመገንባት፣ ለከፋ የማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ወገኖችን መደገፍ ጨምሮ በወንዝ ዳርቻ ስራዎች ከበጋ እስከ ክረምት በዘለቀው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተሳትፎ ላደረጉት ነው እውቅና የተሰጠው፡፡

በዚህም መሰረት በሰርተፍኬት ደረጃ 3 መቶ 67 ተሸላሚዎች፤በነሀስ ደረጃ ከ 5 ሚሊየን እስከ 9 ሚሊየን ብር የለገሱ 35 ተሸላ

ሚዎች፤ ከ10 ሚሊየን እስከ 50 ሚሊየን ብር የለገሱ 44 ተሸላሚዎችን በብር ደረጃ፤ ከ50 ሚሊየን እስከ አንድ መቶ ሚሊየን ብር የለገሱ 14 የወርቅ ተሸላሚዎች፤ ከአንድ መቶ ሚሊየን ብር ጀምሮ ከ4 መቶ 67 ሚሊየን ብር በላይ የለገሱ 12 ተሸላሚዎች በፕላቲኒየም ደረጃ እውቅና ያገኙ ናቸው፡፡

በመርሀ ግብሩ ሁለንተናዊ የድጋፍ ማእቀፎችን ሲያደረግ የቆየው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከ 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በማበርከት የአመቱ ልዩ ተሸላሚ ለመሆንም ችሏል፡፡

በሚካኤል ህሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review