ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቁ በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ላይ የጎርፍ አዳጋ እንዳያጋጥም ለመከላከል አግዟል ሲሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቁ በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ላይ የጎርፍ አዳጋ እንዳያጋጥም ለመከላከል አግዟል ሲሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ

AMN ጥቅምት 21/2018

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቁ በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ላይ የጎርፍ አዳጋ እንዳያጋጥም ለመከላከል አግዟል ሲሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የውሃና ኢነርጂ ሳምንትን ምክንያት በማድረግ ምሁራንና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበትን የፖናል ዉይይት በአዲስ አባባ ሳይንስ ሙዚየም በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በኢትዮጽያ ውሃና ኢነርጂ ሀብት ማልማትና ማስተዳደር ዙሪያ በተገኙ ውጤቶችና ቀጣይ የዘርፉን አቅጣጫ አስመልክቶ በተዘጋጀዉ የዉይይት መድረክ ላይ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በድንበር ተሻጋሪ ወንዞቻችን ጉዳይ ኢትዮጵያ ያላት ጽኑና የማይቀር አቋም የቀጠናውን ተገቢ፣ሚዛናዊና ፍትሀዊ የውሃ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው ብለዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቁ በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ላይ የጎርፍ አዳጋ እንዳያጋጥም ከመከላከሉም በላይ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽኖ የማይበገር አካባቢ የመፍጠር ዕድል መፍጠሩንም ጠቁመዋል፡፡

ህዳሴ መገደቡ ለተፋሰሱ ሀገራት ውሃ ያጎደለ አልነበረም ያሉት ሚኒስትሩ ይህም የሃገሪቱን ውሃን በፍትሃዊነትና በተገቢነት የመጠቀም አቋም የሚገልጽ ነው ማለታቸዉን የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለኤኤምኤን ዲጂታል ሚዲያ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review