በቻይና በቤጂንግ እና ሆንዙ በተካሄደው ማራቶን ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል።
በሆንዙ የማራቶን ውድድር በሴቶች አትሌት ሩቲ አጋ በ2:24:29 ውድድሩን አሸንፋለች ።
በወንዶች አትሌት ጫሉ ደሶ በ2:11:15 በቀዳሚነት አጠናቋል ።
በቤጂንግ በተካሄደው ማራቶን ውድድር በወንዶች አትሌት ለሚ ብርሃኑ 2:08:10 በመግባት ሲያሸንፍ አትሌት ደሳለኝ ግርማ ሁለተኛ ወጥቷል።
በሴቶች አትሌት አንቻሉ ደሴ በ2:26:06 በቀዳሚነት አጠናቃለች ።
ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ቁፍቱ ጣሂር ሦስት መዉጣቷን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።