ለፖሊስ አመራሩ በተሰጠው የሊደርሽፕ ቻሌንጅ ስልጠና የኦፕሬሽን አቅም በማሳደግ በሽብር ቡድኖች ላይ የተሳካ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ መቻሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

You are currently viewing ለፖሊስ አመራሩ በተሰጠው የሊደርሽፕ ቻሌንጅ ስልጠና የኦፕሬሽን አቅም በማሳደግ በሽብር ቡድኖች ላይ የተሳካ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ መቻሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

AMN ጥቅምት 25/ 2018 ዓ.ም

በተጠናቀቀው ሩብ ዓመት ለፖሊስ አመራሩ በተሰጠው የሊደርሽፕ ቻሌንጅ ስልጠና የኦፕሬሽን አቅም በማሳደግ በሽብር ቡድኖች ላይ የተሳካ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ መቻሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

የኢትየጵያ ፌደራል ፖሊስ የ2018 ዓ.ም የአንደኛ ሩብ ዓመት የማጠቃለያ ግምገማ እያካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ‎በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር በተጠናቀቀው ሩብ ዓመት ለፖሊስ አመራሩ በተሰጠው የሊደርሽፕ ቻሌንጅ ስልጠና የኦፕሬሽን አቅም በማሳደግ በሽብር ቡድኖች ላይ የተሳካ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ሀገራችን ያካሄደቻቸው ታላላቅ ሀገራዊ፤ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁነቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመታጠቅና የሰለጠነ የፖሊስ ሠራዊት በማሰማራት በስኬት እንዲጠናቀቁ መቻሉን ገልጸዋል።

በቀጣይም የሎጂስቲክ አቅምን ከዚህ በበለጠ በማሳደግ ዘመናዊ የሆኑ የትጥቅና የተሸከርካሪ አቅሞችን ለማሳደግና የሠራዊቱን የመፈጸም አቅም በከፍተኛ ደረጃ ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራል የምርመራ አቅማችንን በማሳደግ የፎረንሲክና ሌሎች የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም የፍትህ ስርዓቱ እንዲዘምን በማድረግ በሀገርና በሕዝብ ሀብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ የነበሩ የሙስና እና ሌሎች ወንጀሎችን በከፍተኛ ደረጃ በመቆጣጠር በሩብ ዓመቱ በቢሊዮን ብር የሚገመት ሀብት ማዳን ችለናል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር አቅሙን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሳደግ በPHD ፕሮግራም ለማስተማር በዝግጅት ላይ እንዳለ አንስተዋል።

የሠራዊቱን የኦፕሬሽን አቅም ለማሳደግም የልዩ ኮማንዶ ማሰልጠኛ ማዕከልን በመገንባት በፖሊስ ታሪክ የመጀመሪያ የሆኑትን የልዩ ኮማንዶ ሰልጣኞችን በቅርቡ የሚያስመርቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራል በአንዳንድ የፖሊስ አባላት ላይ የሚታዩ የሥነ-ምግባር ክፍተቶችን ለማስተካከልና በቀጣይ እንዳይደገሙ ለማድረግ እየተወሰዱ ያሉ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጨምረው መግለጻቸዉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review