የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር አመራሮች በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የስራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ለነበሩት ለአቶ ጥራቱ በየነ የክብር አሸኛኘት አድርገዋል፡፡
አመራሮቹ አቶ ጥራቱ በየነን በአዲስ አበባ የአመራርነት ቆይታቸዉ ለነበራቸዉ አስተዋፅኦ በማመስገን በሄዱበት መልካሙን ሁሉ በመመኘት በክብር ሸኝተዋቸዋል ።
በተመሳሳይ መልኩ የከተማዉ አመራሮች በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የስራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ለተሾሙት አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል ማድረጋቸዉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡