የአካባቢን ፀጋ መለየትና የስራ አማራጮችን ማስፋት ስራ አጥ ዜጎች ስራ እንዲኖራቸው ያስችላል

You are currently viewing የአካባቢን ፀጋ መለየትና የስራ አማራጮችን ማስፋት ስራ አጥ ዜጎች ስራ እንዲኖራቸው ያስችላል

AMN- ህዳር 4/2018 ዓ.ም

የአካባቢን ፀጋ በመለየትና የስራ አማራጮችን በማስፋት ስራ አጥ ዜጎች ስራ እንዲኖራቸውና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻሉን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

ክፍለ ከተማው በአንድ ጀምበር የስራ እድል ፈጠራ መርሐ ግብር ለ1ሽህ 500 ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ወደ ስራ የማሰማራት መርሃ ግብር አከናውኗል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ምስክር ነጋሽ (ዶ/ር)፣ የከተማ አስተዳደሩ በነደፋቸው ሰው ተኮር ተግባራት ዜጎችን በስራ እድል ተጠቃሚ እያደረጉ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

በእድገት እና በማንሰራራት ላይ በምትገኝ ሀገር የወጣቶች ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው፣ በክፍለ ከተማው ያሉ ፀጋዎችን በመለየት በአንድ ቀን ጀምበር 1ሺ 500 የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችን የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አበበ ተቀባ በበኩላቸው፣ ከዚህ ቀደም የነበረውን የአመለካከት ችግር በመስበር ዜጎች ስራ ወዳድ እንዲሆኑ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን አንስተው፣ ዜጎችን በእድገት ተኮር የስራ ዘርፎች ተጠቃሚ ማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ እንሚቀጥል ገልፀዋል።

የስራ ባሕልና ምርታማነትን በመጨመር የዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጥን እንገኛለን ያሉት የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራአስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘመን ተስፋዬ፣ ስራ እድል የተፈጠረላቸው ተጠቃሚዎች አስፈላጊው ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ተናግረዋል።

በእለቱም ስራ እድል የተፈጠረላቸው ተጠቃሚዎች ከዚህ ቀደም በስራ እጦት ሲቸገሩ መቆየታቸውን ገልፀው፣ ክፍለ ከተማው ያዘጋጀው የአንድ ጀምበር የስራ እድል ፈጠራ ሕይወታቸውን ለመለወጥ የሚያስችላቸው መሆኑን ገልፀዋል።

በታምሩ ደምሴ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review