መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር ፣ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ብሎም ሀገርን ለማሻገር በጋራ መስራት ይጠበቅባቸዋል

You are currently viewing መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር ፣ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ብሎም ሀገርን ለማሻገር በጋራ መስራት ይጠበቅባቸዋል

AMN – ህዳር 5/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ማስጠበቅ የሚያስችል ጥቅም ያለቸውን የመገናኛ ተቋማትን እና ጋዜጠኞችን ለመፍጠር የኢትዮጵያ የልህቀት ማዕከል ስራ ማስጀመሩ ይታወቃል ።

የልህቀት ማዕከሉ የብሔራዊ ጥቅም የህብረብሔራዊ አንድነት የወል ትራክትና ብልጽግና ላይ የጋራ አቋም ያላቸው የመገናኛ ብዙሓን ተቋማትና ጋዜጠኞችን ለማፍራት ያለመ ነው ።

ማዕከሉ 2ኛውን ዙር መገናኛ ብዙሃንና ዲሞክራሲ ላይ የሚያተኩር ስልጠና አስጀምሯል።

በስልጠናዉ ላይ የተገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስቴር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በሀገራዊ ዕይታ ዙሪያ ከፍ ያለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ከማድረግ ረገድ ስልጠናው ወሳኝ ሚና ያለዉ መሆኑን አንስተዋል፡፡

አቶ ተስፋዬ፣ “እንዲህ አይነት ስልጠናዎች ሀገራዊ እይታዎችን ከፍ ያደርጋሉ ያሉ ሲሆን፣ እንደ ሀገር የጀመርናቸውን ስራዎች በጋራ ማሳካት እንድንችል የሚያቀራርብንና የሚያግባቡን መድረኮች ሆነው ያገለግላሉ” ብለዋል።

አክለውም የሀገር ግንባታ እውን እንዲሆን እያንዳንዱ አካል የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

መገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር ፣ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር ብሎም ሀገርን ለማሻገር በጋራ መስራት እንዳለባቸው ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ ሚዲያዎች 5 ዋና ዋና ጉዳዮችን ማእከል አድርገው ቢሰሩ ኢትዮጵያን ማሻገር እንደሚቻል አንስተዋል፡፡

ሚዲያዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ መደራደር እንደሌለባቸው ፣ ህብረብሔራዊ አንድነት እና አሰባሳቢ ትርክትን እንዲሁም የዲሞክራሲ ባህል እና የተቋም ግንባታን ማጠናከር፤ በአዎንታዊ የሰላም ባህል ግንባታ እና የኢኮኖሚ ሉአላዊነት ላይ በጋራ መስራት እንደሚጠበቅባቸዉ አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮነን (ዶ/ር) የልህቀት ማዕከሉ ብሔራዊ ጥቅምን ማእከል ያደረገ ፣ ለብሔራዊ ጥቅም ቅድሚያ የሚሰጥ እና በዚያ ቅኝት የሚሰራ ባለሞያን ለመፍጠር አላማ አንርጎ እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የልህቀት ማእከሉ ጋዜጠኝነትን እና የሚዲያ ተግባራትን እውን የሚያደርጉ እና የተካኑ የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎችን ለማፍራት እንዲያግዝ ታስቦ መሰራቱን ገልጸዋል።

በስልጠናዉ ላይ የተገኙ የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች በበኩላቸው የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በውል ተረድተው ማስጠበቅ እንዲችሉ ስልጠናዉ ትልቅ እድል እንደፈጠረላቸው ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review