የጤና ሚኒስቴር በደቡበ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ የሄሞራጅከ ፊቨር (Viral Hemorragic Fever) በሽታ መከሰቱን እና የበሽታዉን ምንነት በማረጋገጥ ላይ መሆኑን መግለጹ ይታወቃል፡፡
ሚኒስቴሩ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የበሽታዉ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን መለየት መቻሉን መግለፁ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎ የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም በደቡብ ኢትዮጰያ ክልል የተከሰተውን የሄሞራጅክ ፊቨር በሽታ ለመቆጣጠር የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ ነው ሲሉ ገልፀውታል።

ዋና ዳይሬክተሩ በማህበራዊ ትስስር ገፆቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፣ ኢትዮጰያ በደቡብ የአገሪቱ ክፍል 9 ሰዎች ያጠቃውን በሽታ የማርበርግ ቫይረስ መሆኑን ማረጋገጧን ገልፀዋል።
በኢትዮጰያ የተከሰተውን በሽታ ፈጣንእና ግልፅ ምላሽ ለመስጠት የጤና ሚንስቴር፣የኢትዮጰያ ህብረተሰብ ጤና ኢንልቲትዮት እና የክልሉ የጤና ቢሮ ያደረጉትን ጥረት ዋና ዳይሬክተሩ አድንቀዋል።
ይህ እርምጃ ኢትዮጰያ ወረርሽኑ በፍጥነት ለመቆጣጠር ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ አድናቆታቸውን ባሰፈሩት መልክት ገልፀዋል።
የአለም የጤና ድርጅት በየደረጃው ባሉ ቅርጫፎቹ በሽታውን ለመቆጣጠር እና የተያዙ ሰዎችን ለማከም በንቃት እየደገፈ መሆኑን ገልፀው፣ ድንበር ተሻጋሪ ስርጭትን ለመቋቋም የሚደረገውን አጠናክሮ እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
በሄለን ተስፋዬ