የኮሪደር ልማት የጉስቁልና መገለጫ የነበሩ መልኮችን በመቀየር የከተሞችን የእድገት መሪነት ያሳየ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ተናገሩ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የጀመረው የኮሪደር ልማት ለኢትዮጵያ ከተሞች ብሎም ለአፍሪካ ከተሞች አብነት መሆኑንም ተናግረዋል።
በ10ኛው የከተሞች ፎረምም ይህ አብነት በጉልህ መታየቱን ነው ሚኒስትሯ የገለጹት።
የዜጎችን ኑሮ በማሻሻል፣ የስራ እድል ፈጠራን በማስፋት፣ የከተማ ፕላን ደረጃን በማስጠበቅ አይተኬ ሚና መጫወት ተችሏልም ነው ያሉት።
የኮሪደር ልማቱ ከተሞችን አገልግሎትን በፋትሃዊነት እንዲሰጡ ማስቻሉን የጠቆሙት ሚኒስትሯ፣ አዳዲስ ኢኮኖሚ የተፈጠረበት ነው ብለዋል።
10ኛው የከተሞች ፎረምም እነዚህን ጸጋዎች በማስተዋወቅ፣ ከተሞች እርስ በርስ መወዳዳርና መተባባር የቻሉበት እንደሆነ ሚኒስትሯ ጠቁመዋል። በፎረሙ 150 ከሚሆኑ ከተሞች የተውጣጡ ከ 7 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ታድመውበታል።
ፎረሙ በኤግዚብሽንና በፓናል ውይይት እየተከበረ ነው።
በፈቃዱ መለሰ
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን ምርጫዎ ያድርጉ ! የትዉልድ ድምጽ ! https://linktr.ee/AddisMediaNetwork