በአዲስ አበባ በመከናወን ላይ የሚገኘዉ የኮሪደር ልማት የሀገሪቱን የስራ ባህል በእጅጉ የቀየረ ነው

You are currently viewing በአዲስ አበባ በመከናወን ላይ የሚገኘዉ የኮሪደር ልማት የሀገሪቱን የስራ ባህል በእጅጉ የቀየረ ነው

AMN – ህዳር 9/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ 24/7 በመከናወን ላይ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የሀገሪቱን የስራ ባህል በእጅጉ የቀየረ መሆኑን የኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ተዋበ ገድሌ ገለጹ፡፡

የሸማቾች መብት ጥበቃ የሲቪክ ማህበር የኢንቨስትመንት አማካሪ የሆኑት አቶ ተዋበ ገድሌ አዲስ አበባ ከተማ ከዚህ ቀድሞ የነበራትን እና አሁኑ ላይ ያላት ገጽታ ልዩነቱ የጎላ መሆኑን እና የስራ ባህሏም በእጅጉ መቀየሩን ከኤ ኤም ኤን የሚሰሩ እጆች ወግ ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

አክለውም በከተማዋ የተተገበሩት የኮሪደር ልማት ስራዎች ፍጥነት ከተማዋ እያስመዘገበችው ያለው ሁለንተናዊ ለውጥ አንዱ ማሳያው መሆኑን አንስተው፤ ለዚህም የአመራሮች ቁርጠኝነት እና ጥበብ ጉልህ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በምሽት መስራት ያልተለመደ ተግባር መሆኑን ያነሱት አማካሪው፣ የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን የስራ ባህል በእጅጉ የቀየረ ሲሆን ለበርካቶችም የሥራ እድል የፈጠረ መሆኑን አመላክተዋል።

ኢንቨስትመንት ሶስት አንኳር ነገሮች እንዳሉት ያነሱት አማካሪው አቶ ተዋበ ፤ እሴትን መጨመር ፣ የስራ እድልን መፍጠር እና የቴክኖሎጂ እና የክህሎት ሽግግርን መፍጠር መሆኑን በቆይታቸው አንስተዋል።

ሌላኛው የውይይቱ ተሳታፊ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን የልጆች ፕሮግራም አዘጋጅ ወገን ክብረአብ እንደተናገረው፣ ትምህርት ሀገርን የሚቀይር መሆኑን እና ልጆች ጠንክረው እንዲማሩ ልጆች ላይ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው!

በዚህም የሚሰራ ትውልድ መፍጠር መቻሉን ገልፀው፣ ለትውልዱ ስራ የመስራት ባህልን በማውረስ የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ የገባል ሲሉ አቶ ተናግረዋል፡፡

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review