ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሴሪ አንዋር ኢብራሂም ለሶስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ወደ ምድረቀደምት ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ በማለት ገልጸዋል፡፡
ጉብኝትዎ በማሌዢያ እና ኢትዮጵያ መካከል እያደገ ያለውን ወዳጅነት እና ትብብር የሚያሳይ ሲሆን በሀገራችን የብልጽግና ጉዞ ውስጥም በጠቃሚ ጊዜ የተደረገ ጉብኝት ነው ብለዋል፡፡