በዓለም ላይ ፈጣን እድገት በማስመዝገብ ላይ የምትገኘዉ ማሌዢያ እና ዋና ከተማዋ ኳላ ላምፑር

You are currently viewing በዓለም ላይ ፈጣን እድገት በማስመዝገብ ላይ የምትገኘዉ ማሌዢያ እና ዋና ከተማዋ ኳላ ላምፑር

AMN ህዳር 10/2018

የማሌዢያ ዋና ከተማዋ ኳላላምፑር የኮሪደር ልማት ስራዎችን ከቱሪዝም እና ንግድ ከባቢዎች ጋር በማስተሳሰር ረገድ ውጤታማ ስራ በማከናወን ትታወቃለች።

ማሌዥያ በአለም ላይ በፈጣን እድገት ላይ የምትገኝ ሀገር ነች።

ሀገሪቱ በኢንዱስትሪ፣ ግብርና፣ ማዕድንና አገልግሎት ዘርፎችን መሰረት ያደረገ የብዝሃ ኢኮኖሚ አቅጣጫዎችን በመከተል ውጤታማ ስራ በማከናወን ትታወቃለች።

ማሌዢያዎች በተለይ በፓልም ዘይት፣ የጎማ ምርትና አካባቢ ጥበቃ የተሻለ ልምድ እንዳላቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች የልዑካን ቡድን ከአንድ አመት በፊት በማሌዢያዋ ዋና ከተማዋ ኳላላምፑር ባደረጉት ጉብኝት በተለያዩ ዘርፎች አብረዉ ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በኳላ ላምፑር የተሠሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች በኢትዮጵያ ከተሞች እየተከናወኑ ላሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች ትምህርት የሰጠ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በወቅቱ ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሒም ጋር ባደረጉት ዉይይት የሁለትዮሽ ግንኙነትን ከማጠናከር ባሻገር በከተማ ልማት ልምድ ለመቅሰም ተስማምተዋል።

ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን የንግድ ትስስር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተመሳሳይ ዉይይት አድርገዋል።

በማሌዢያ ኳላ ላምፑር ተደርጎ በነበረዉ የሥራ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል በኢንቨስትመንት ያሉ ምቹ እድሎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን የማሌዥያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ባሉ ምቹ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቦ ነበር።

የማሌዥያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሒም የሁለትዮሽ ግንኙነቱ እንዲጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ያረጋገጡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አንዋር ኢብራሒም ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ግብዣ ማቅረባቸዉ ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ማሌዥያ ኦፊሴላዊ ጉብኝት ካደረጉ አንድ ዓመት በኋላ፣ የማሌዥያ ፌዴሬሽን ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ገብተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ጉብኝትና የልምድ ልውውጥ ጥልቅ አጋርነታቸዉን የሚመሰክር መሆኑን እና ይህም በርካታ ቁልፍ ሰነዶችን በመፈረም መጠናከሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመግባቢያ ሰነዶቹ በቱሪዝም፣ በጤና፣ በአየር ትራንስፖርት አገልግሎት፣ በኳላ ላምፑር ከተማ ምክር ቤት እና በአዲስ አበባ አስተዳደር የትብብር መስክ ላይ ያተኮሩ መሆናቸዉን ገልጸዋል።

በተደረገዉ የሁለትዮሽ ውይይት፣ ሁለቱ ሃገራት ትብብራችንን የበለጠ ለማጠናከር እና ለማስፋት ያላቸዉን የጋራ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉት የማሌዥያ ፌዴሬሽን ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤና ከመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን የአድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

በአዲስ አበባ በተካሄደዉ የኢትዮጵያ ማሌዢያ ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም ላይ ተገኝተዉ ንግግር አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኳላ ላምፑር ከተማ ምክር ቤት እና በአዲስ አበባ አስተዳደር መካከል ያደረጉትን ትብብር ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከማሌዥያዋ ኳላ ላምፑር ከተማ ጋር የእህትማማችነት የትብብር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸዉን ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ :- ጠቅላይ ሚኒስትር (ዶ/ር) ዐቢይ አሕመድ እና የማሌዥያ ፌዴሬሽን ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂም በተገኙበት ፤ በማሌዥያዋ ኳላ ላምፑር ከተማ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መካከል የእህትማማችነት የትብብር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ ስምምነት አዲስ አበባ እና ኳላላምፑር : ኢትዮጵያና ማሌዢያ በተለያዩ ዘርፎች ያደረጓቸዉን ግንኙነቶች ይበልጥ የሚያጠናክር ነዉ።

በወንድማገኝ አሰፋ

#አዲስሚዲያኔትዎርክ

#addisababa

#Ethiopia

#linkaddis

#KualaLumpur

#amn

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review