ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከአዲሱ የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት ዶክተር ሲዲ ኡልድ ታህ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ከአዲሱ የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት ዶክተር ሲዲ ኡልድ ታህ ጋር ተገናኝተን ተወያይተናል። ውይይታችን ባንኩ በመላው አፍሪካ አካታች እድገት እንዲኖር የሚያደርገውን ወሳኝ ሚና ያጠናከረ ነበር ብለዋል፡፡