ዓለም አቀፍ የህፃናት ቀን የሕፃናት ጥበቃ እና የመጫወት መብት ለሁሉም ሕፃናት በሚል ሐሳብ በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው።
በአሉ በዓለም ለ36ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ ነው እየተከበረ የሚገኘው ፡፡
በባአሉ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ ሮ ቆንጂት ደበላ፤ ጨዋታ ለልጆች የዕድገታቸው መሳሪያና የህይወታቸው መሰረት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ጨዋታ ለህፃናት ቅንጦት ሳይሆን ልክ እንደ ምግብና መጠጥ የዕለት ከዕለት ተግባራቸው እና መሰረታዊ ፍላጎታቸውም ብለዋል፡፡
ህፃናትን መጠበቅና መንከባከብ የወላጆች ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት እና ግዴታ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ህፃናት መብታቸውና ፍላጎታቸው ተጠብቆ እንዲያድጉ ለማድረግ በቀዳማይ ልጅነት መርሃ ግብር ቀርፆ እየሰራ ያለው ስራ ውጤታማ እየሆነ እንዳለም ገልፀዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ የህፃናት ማቆያን ጨምሮ የተሰሩ መሰረተ ልማቶች ከተማዋ ህፃናት ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች መሆኑን ማሳያ ስለመሆኑም አንስተዋል።
በጺሆን ማሞ