ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የከተማዋን የቱሪዝም አቅም ለማጎልበትና ለዓለም ለማስተዋወቅ የላቀ ፋይዳ እንዳለው ተገለጸ

You are currently viewing ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የከተማዋን የቱሪዝም አቅም ለማጎልበትና ለዓለም ለማስተዋወቅ የላቀ ፋይዳ እንዳለው ተገለጸ

AMN ህዳር 13/2018

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአዲስ አበባን የቱሪዝም አቅም ለማጎልበትና ለአለም ለማስተዋወቅ የላቀ ፋይዳ እንዳለው የአዲስ አበባ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ገለጸ።

ቢሮው በነገው እለት በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሔደውን ታላቁ ሩጫን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የቢሮው ኃላፊ አቶ ሐፍታይ ገ/እግዚአብሔር በመዲናዋ የሚካሔደው ታላቁ ሩጫ የህዝቦችን አድነትና ማህበራዊ መስተጋብርን በማጎልበት ረገድ ያለው ፋይዳ ክፍተኛ ነው ብለዋል።

የዘንድሮው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከተማዋ ከመቼውም ጊዜ በላይ በተዋበችበት ወቅት መካሔዱ ለቱሪዝሙ ዘርፍ የሚያበረክተው አስተዋጽኦም የጎላ እንደሆነም ገልጸዋል።

አዲስ አበባ ከኮንፍረስ ቱሪዝም ባሻገር የስፖርት ቱሪዝምን ማከናወን የሚያስችል አቅምንም ገንብታለች ብለዋል።

በታለቁ ሩጫ ለመሳተፍ ወደ ከተማዋ የመጡ እንግዶችም በመዲናዋ የተከናወኑ መሰረተ ልማቶችንና የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለአለም በማስተዋወቅ የበኩላቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

የከተማዋ ነዋሪዎችም በተለመደው የእንግዳ ተቀባይነት ባህል እንግዶች የተሳካ ጊዜን እንዲያሳልፉ የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

በ ሄኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review