ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ ጋር በአለምአቀፍ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ብሎም በቁልፍ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸዉን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት በቡድን 20 ጉባኤ ያደረኳቸውን ሁለትዮሽ ውይይቶቼ የመጨረሻ የሆነውን ውይይት ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ ጋር በአለምአቀፍ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ብሎም በቁልፍ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ አተኩረን አከናውነናል ሲሉ ገልጸዋል።