የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት 41 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የዋጋ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን ገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የፀረ-ኮንትሮባንድ ፖሊስ መምሪያ የሬጅመንት 4 አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ጀማል ደቀቦ መነሻውን ጅቡቲ መዳረሻውን አዲስ አበባ አድርጎ ኮንትሮባንድ ጭኖ በመጓዝ ላይ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኢት. A 34228 ተሽከርካሪ በሞጆ ከተማ ተጠርጣሪዎቹ ከነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ዋና ኢንስፔክተሩ ገልፀል፡፡
በቅንጅት በተደረገው ጠንካራ የኦፕሬሽን ሥራ መድኃኒቶች፣ ልዮ ልዮ አልባሳት፣ የሞባይል ቻርጀሮች፣ ባትሪዎች፣ ሲጋራና ሽቶ በኤግዚቢትነት ተይዘው በአዳማ እና በአዋሽ ሰባት ጉሙሩክ ቅርንጫፍ መጋዘን ገቢ ገቢ መደረጋቸውንም ዋና ኢንስፔክተር ጀማል መናገራቸዉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል፡፡