በተባበሩት መንግሥታት የአየርንብረት ለውጥ ማሕቀፍ ኮንቬንሽን መሠረት የኢትዮጵያ የኮፕ 32 አስተናጋጅ ሀገር መሆኗን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ጌዲዮን ጢሞቴዎስን (ዶ/ር) የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝደንት አድርጎ መመደቡን ሲገልጽ ደስታ ይሰማዋል።
ዶክተር ጌዲዮን ከሀገር ውስጥ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከተባበሩት መንግሥታት አካላት እና አለምአቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር የኮፕ 32 ዝግጅትን የሚመሩ ይሆናል።
የኢትዮጵያ መንግሥት የተባበሩት መንግሥታት የአየርንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ኮንቬንሽን አባል ሀገራት ለኢትዮጵያ የማዘጋጀት ኃላፊነት በመስጠታቸው ምስጋናውን እያቀረበ በጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) አስተባባሪነት ከአለም የአየር ንብረት ጥበቃ ማኅበረሰብ ጋር በቅርበት ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን መግለጹን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡