ባርሰሎና አትሌቲኮ ማድሪድን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ

You are currently viewing ባርሰሎና አትሌቲኮ ማድሪድን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ

AMN ኅዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም

በስፔን ሱፐር ካፕ ጨዋታ ምክንያት ቀድሞ የተደረገው የባርሰሎና እና አትሌቲኮ ማድሪድ ጨዋታ በባርሰሎና 3ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

እየታደሰ በሚገኘው ካምፕ ኑ በተከናወነው ጨዋታ ራፊና ፣ ዳኒ ኦልሞ እና ፌራን ቶሬስ የካታሎኑን ክለብ ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።

የአትሌቲኮ ማድሪድን አንድ ግብ አሌክስ ባኤና አስቆጥሯል።

ባርሴሎና ድሉን ተከትሎ ነጥቡን 37 አድርሶ መሪነቱን አስቀጥሏል።

ነገ ከሚጫወተው ሪያል ማድሪድ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አራት አስፍቷል።

ከአምስት ተከታታይ የላሊጋ ድል በኋላ እጅ የሰጠው የዲያጎ ሲሞኔው አትሌቲኮ በ31 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review