ቼልሲ በሊድስ ሲሸነፍ ፣ ሊቨርፑል ከሰንደርላንድ ነጥብ ተጋርቷል

You are currently viewing ቼልሲ በሊድስ ሲሸነፍ ፣ ሊቨርፑል ከሰንደርላንድ ነጥብ ተጋርቷል

AMN ኅዳር 25/ 2018 ዓ.ም

ቼልሲ ከሜዳው ውጪ ሊድስ ዩናይትድን ገጥሞ 3ለ1 ተሸንፏል። ጃካ ቢዮል ፣ አኦ ታናካ እና ዶሚኒክ ካልቨርት ሌዊን የሊድስን ግቦች አስቆጥረዋል።

ተቀይሮ የገባው ፔድሮ ኔቶ የቼልሲን ብቸኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል። የዋንጫ ተፎካካሪ መስሎ የነበረው ቼልሲ በሽንፈቱ ምክንያት ከመሪው አርሰናል በዘጠኝ ነጥብ እርቋል።

በአንፊልድ ሰንደርላንድን ያስተናገደው ሊቨርፑል ጨዋታውን 1ለ1 አጠናቋል። ቼምሰዲን ታልቢ ሰንደርላንድን ቀዳሚ ቢያደርግም ኖርዲ ሙኪዬሌ በራሱ ላይ ያስቆጠረው ግብ ሊቨርፑልን አቻ አድርጓል።

አስተማማኝ ብቃት ማሳየት የተሳነው ሊቨርፑል የፊታችን ቅዳሜ ከሊድስ ጋር ይጫወታል። በቀጣይ ሳምንት አጋማሽ በቻምፒየንስ ሊጉ ኢንተር ሚላንን በሳን ሲሮ የሚገጥም ይሆናል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review