በአዲስ አበባ እየተመዘገበ ያለውን ሁለንተናዊ ለዉጥ ለማስቀጠል ተጠሪነቱ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት የሆነ 7 ክላስተር ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ ተገለጸ።
ቅንጅታዊ አሠራርን በማጠናከር ጥራትና ፍጥነትን ለመጨመር ታቅዶ የተቋቋመው ክላስተሩ ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ ላይ ትኩረት በማድረግ ይሠራል።
የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ እንዳሉት በተበታተነ መልኩ የሚሠሩ ተቋማት በመቀራረብ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን እንዲቀርፉ ክላስተሩ አቅም ይፈጥራል።
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ፥ የአዲስ አበባ ሰላም ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ፥ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እና የአዲስ አበባ ደምብ ማስከበር ባለስልጣንን ጨምሮ አሥራ አምስት ተቋማት የቅንጅት ሥራ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።
በአልማዝ ሙሉጌታ