አመራሩ የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን ወደ ዕድል በመቀየር ለላቀ ስኬት መትጋት አለበት

You are currently viewing አመራሩ የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን ወደ ዕድል በመቀየር ለላቀ ስኬት መትጋት አለበት

‎AMN ሕዳር 28/2018 ዓም

‎አመራሩ የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን ወደ ዕድል በመቀየር ለላቀ ስኬት መትጋት እንዳለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

‎“በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ ለተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው 3ኛ ዙር የወረዳ አመራሮች ስልጠና ተጠናቋል።

‎ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማጠቃለያው ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በሀገራችንና በመዲናዋ እየተመዘገቡ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ድሎች አመራሩ እና ሕዝቡ በቅንጅት ሰርተው ያሳኳቸው ናቸው ብለዋል።

‎ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ አረንጓዴ አሻራ፣ የስንዴ ልማትና የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በሀገራችንና በአዲስ አበባ የተመዘገቡ አስደናቂ ለውጦች ለበለጠ ሥራ የሚያነሳሱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

‎የአመራር ስልጠናው በአዲስ ዕይታ ለተጨማሪ ስኬት መትጋት የሚያስችል የእውቀትና የአመለካከት አቅም የተፈጠረበት እንደሆነም ገልጸዋል።

‎አመራሩ የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን ወደ ዕድል በመቀየር ለላቀ ውጤት መትጋት እንዳለበት ያነሱት ከንቲባ አዳነች በሁሉም ዘርፍ አርዓያ ሊሆኑ የሚችሉ ሥራዎችን መሥራት እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።

‎ለዚህም በማያቋርጥ የአመለካከት፣ የስነምግባርና የባህሪ ግንባታ ራስን ማብቃት አስፈላጊ መሆኑን አጽንዖት ሰጥተዋል።

‎ስልጠናው በግብርናና ገጠር ትራንስፎርሜሽን፣ በኢንዱስትሪ፣ በከተማ ልማትና በቱሪዝም ዘርፎች ላይ ያተኮረ መሆኑን አንስተው ስልጠናው በተሰናሰለ የዘርፎች እመርታ መዋቅራዊ ሽግግርንና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማሳካት መግባባት የተፈጠረበት ነው ብለዋል።

‎ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተቀመጡ ሀገራዊ ግቦችን ለማሣካት አመራሩ በመፍጠርና መፍጠን መርህ መሥራት እንደሚጠበቅበትም

‎የከነቲባ ጽሕፈት ቤት ገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review