ከንቲባ አዳነች አቤቤ “ከህዝብ ጋር በተደረገው ውይይት የተሰጡትን ጥቆማዎችን በመጠቀም ማጣራት ማድረጋቸውን አስታውሰዋል ፡፡

ይህም በመደረጉ የነዋሪዎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉንና በተለይም ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባ የተዘነጉ፣ ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውን አቅመ ደካማ ወገኖችን እንባ ማበስ መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል ፡፡

ከንቲባዋ ነዋሪዎች ከነበሩበት አስከፊ ሕይወት በመታደግ ነገን በተስፋ እንዲያዩ የሚያስችል ስራ መሰራቱን ከንቲባ ፅህፈት ቤት ባጋራው መረጃ ጠቁሟል ፡፡