አዲስ አበባ ከተማ እንግዳ ተቀባይ ብቻ ሳትሆን የበርካታ ኤምባሲዎች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ መሆን በመቻሏ ከዓለም ትላልቅ የዲፕሎማሲ ከተሞች አንዷ እንድትሆን አስችሎታል፡፡
መስህብነትን የተላበሱ መንገዶቿ፣ ህንፃዎቿ ፣አረንጓዴ ስፍራዎቿ እና ግዙፍ አለም አቀፍ ሁነቶችን ማስተናገድ የሚችሉ ማዕከላቶቿ ጨምሮ ሁሉንም ታሳቢ ያደረጉ የቱሪስት መዳረሻዎቿ ተመራጭ እና ተወዳጅ ከተማ እንድትሆን ያደረጓት ልዩ ገፀ-በረከቶች ናቸዉ፡፡

ከተማዋ አሁን ላይ በርካታ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ጉባኤዎችን በብቃት እንደምታስተናግድ በቅርብ ያካሄደችው ትላልቅ ጉባኤዎችና ስብሰባዎች ማሳያ ሲሆኑ ባሳለፍነው ዓመት ብቻ 150በላይ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን በስኬት በማከናወን ተመራጭ ከተማ መሆኗን አረጋግጣለች ፡፡
በዚህም ለበርካታ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ተመራጭ የሆነችው አዲስ አበባ ለአፍሪካዉያን ጭምር ኩራት በመሆን ደማቅ ታሪኳን ፅፋለች፡፡ – የአዲስ አበባ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ