አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያዉ ልሳን እና የሀገር ድል አብሳሪ በመሆን የትዉልድ ድምፅነቱን በተግባር እያረጋገጠ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡
አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ እና የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዋርካን እና መሰል ፕሮግራሞችን በጋራ የሚሰሯቸዉን ስራዎች ለማጠናከር ያለመ የመግባቢያ ስምምነትን ተፈራርመዋል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱን የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀፍታይ ገብረ እግዚአብሄር እና የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ፈርመዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀፍታይ ገብረ እግዚአብሄር አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የአዲስ አበባ የመጀመሪያዉ የመረጃ ምንጭ በመሆን የትዉልድ ድምፅ የመሆን ህልሙን እዉን አድርጓል ብለዋል፡፡
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የህዝብ እና የመንግስት ትክክለኛ ድልድይ ሆኖ እያገለገለ ነዉ ያሉት ሀላፊዉ የአዲስ አበባን ልማት በማጉላት የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶች ተገቢዉ ምላሽ ይሰጣቸዉ ዘንድ በማድረግ በመንግስት መካከል ድልድይ ሆኖ እያገለገለ ነዉ ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ እና አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋርካን እና መሰል የህዝብ አንደበት የሆኑ ስራዎችን በጋራ ይሰራሉ ያሉት አቶ ሀፍታይ በቀጣይም ይህን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ከብቁ የሰዉ ሀይል ጋር አቀናጅቶ የአዲስ አበባ የመረጃ ምንጭ በሃገር አቀፍ ደረጃም ተወዳዳሪ ሚዲያ እየሆነ ነዉ ብለዋል፡፡
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርከ አዳዲስ ይዘቶችን ቀርፆ በሁለት የቴሌቪዥን ቻናሎች በሬድዮ በጋዜጣ እና በድጅታል አማራጮች የህዝብ እና መንግስት አገናኝ ድልድይ ሆኖ እያገለገለ ነዉ ብለዋል፡፡
ሚዲያዉ ከአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል፡፡
በተመስገን ይመር