አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በአይነቱ እና በአቀራረቡ ልዩ የሆነ አዲስ ድራማ ለአድማጭ ተመልካቾቹ ሊያቀርብ መሆኑን አበሰረ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በአይነቱ እና በአቀራረቡ ልዩ የሆነ አዲስ ድራማ ለአድማጭ ተመልካቾቹ ሊያቀርብ መሆኑን አበሰረ

AMN – ታህሳስ 7/2018 ዓ.ም.

የትውልድ ድምጽ የሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በተለያዩ የይዘት አቀራረቦች እና አማራጮች ከሚያዘጋጃቸው ፕሮግራሞች አንዱ የመዝናኛው ዘርፍ ሲሆን፣ ለዚህም ይሆን ዘንድ በአይነቱ እና በአቀራረቡ ልዩ የሆነ አዲስ ድራማ ይዞ ሊቀርብ መሆኑን አብስሯል።

የመዲናዋን ነዋሪ የመዝናኛ አማራጭ እና ተደራሽ የሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በአይነቱ እና በአቀራረቡ ልዩ ስለሆነው አዲሱ ድራማ ዙሪያ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከቴድሮስ ተሾመ /ቴዲ ስቲዲዮ / ጋር በመሆን ውብ አዲስ የሚል ርዕስ ያለው ድራማን ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ በዛሬው ዕለት አመሻሽ 11፡00 ላይ በአራዳ ፓርክ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተለያዩ የኪነ ጥበብ ባለሙዎች በሚገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የትውልድ ድምጽ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review