አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ሀገራዊ ጥቅምን ያስቀደሙ ይዘቶችን በተለያዩ ቋንቋዎች ተደራሽ በማድረግ ተወዳዳሪነቱን አጠናክሮ መቀጠሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ሀገራዊ ጥቅምን ያስቀደሙ ይዘቶችን በተለያዩ ቋንቋዎች ተደራሽ በማድረግ ተወዳዳሪነቱን አጠናክሮ መቀጠሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ

AMN- ታኅሣሥ 9/2018 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ሀገራዊ ጥቅምን ያስቀደሙ ይዘቶችን በተለያዩ ቋንቋዎች ተደራሽ በማድረግ ተወዳዳሪነቱን አጠናክሮ መቀጠሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የክልልና የፌደራል ተቋማት ክትትል ሥራ መሪ አቶ ከበበ ዳዲ ገለጹ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተቋማት ክትትል ቡድን በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በመገኘት ከሰው ሀብት አስተዳደር እስከ ስርጭት ክፍል ያለዉን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ተመልክቷል፡፡

ከምልከታው በኋላም ከኤ ኤም ኤን ማኔጅመንት አባላት ጋር በተቋሙ አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ሀገራዊ ጥቅምን ያስቀደሙ ይዘቶችን በተለያዩ ቋንቋዎች እና የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ተደራሽ በማድረግ የተጣለበትን ህዝባዊና ሃገራዊ ሃላፊነት በብቃት እየተወጣ ይገኛል።

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ እና የቋንቋዎች ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ብዙዓለም ቤኛ፣ ተቋሙ በመዲናዋ በፍጥነት እየተከናወኑ ለሚገኙ የልማት ሥራዎች ሰፊ ሽፋን ሰጥቶ በመስራት የህዝብና የትዉልድ ድምጽ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

ኤኤምኤን ከመዲናዋም አልፎ በሃገር አቀፍ ደረጃ ዘላቂ ሠላምና ልማት እንዲረጋገጥ የበኩሉ ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በሀገር ውስጥ ካሉ ግንባር ቀደም ሚዲያዎች አንዱ መሆኑን ያነሱት ኃላፊዉ ይህንኑ ተወዳዳሪነቱን አጠናክሮ መቀጠሉን አንስተዋል።

በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በምክትል ሥራ አስፈፃሚ ማዕረግ የሀብት አስተዳደር ኃላፊ አቶ ጌታቸው ዳዲ፣ ተቋሙ እየሰራቸው በሚገኙ ሥራዎች ተከታታይ ለውጦችና ስኬቶችን እያስመዘገበ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የክልልና የፌደራል ተቋማት ክትትል ሥራ መሪ አቶ ከበበ ዳዲ፣ ተቋሙ ዲጂታላይዝ ሥርዓት በመዘርጋት የውስጥ አሰራሩን ከወረቀት ነፃ ማድረግን ጨምሮ በርካታ ለውጦችን ተግባራዊ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

የይዘት ሥራዎችንም ከቀረፃ ጀምሮ ተዘጋጅቶ አየር ላይ የሚውልበትን መንገድም ዲጂታላይዝ ማድረጉን የገለጹት አቶ ከበበ፣ በቀጣይ እንደ ሀገር ተግባራዊ ለማድረግ የሚጠበቀውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ሥራ ላይ ማዋል እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከጊዜ ወደ ጊዜ ውጤታማ እየሆነ የመጣ ተቋም መሆኑን በመግለጽ፣ ይህንኑ ተወዳዳሪነቱን በሁሉም ዘርፍ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በቴሌቭዥን: በሬድዮ: በዲጂታል ሚዲያና በአዲስ ልሳን ጋዜጣ በተለያዩ ቋንቋዎችና አቀራረቦች መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ በሃገር ዉስጥ እና በዉጭ ሃገራት ጭምር ተወዳዳሪ ሚዲያ መሆኑ በዉይይት መድረኩ ተገልጿል።

በታምራት ቢሻው

#Ethiopia

#addisababa

#addismedianetwork

#VoiceOfGenerations

#media

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review