በአዲስ አበባ ከተማ የኑሮ ውድነት እና የገበያ ማረጋጋት ግብረ-ኃይል የአንድ ወር የስራ ክንውን እየገመገመ ይገኛል።
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩና የክፍለ ከተሞች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በመዲናዋ በአንድ ወር ውስጥ ምርትና ምርታማነትን እንዲሁም የመሰረታዊ ፍጆታ እቃዎችን የአቅርቦት ምጣኔን ማሳደግን ጨምሮ የኑሮ ውድነትን እና ገበያን ለማረጋጋትን የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።
በሔኖክ ዘነበ