አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በሃገር አቀፍና በከተማ ደረጃ የተያዘዉን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለማሳካት ተሳትፎዉን አጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በሃገር አቀፍና በከተማ ደረጃ የተያዘዉን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለማሳካት ተሳትፎዉን አጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ

AMN -ታሕሣሥ 18 /2017 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በሃገር አቀፍና በከተማ ደረጃ የተያዘዉን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለማሳካት ተሳትፎዉን አጠናክሮ መቀጠሉን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገለጹ።

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋን ጨምሮ የተቋሙ ሌሎች አመራሮችና ሠራተኞች ባለፈው ክረምት በጉለሌ የእጸዋት ማዕከል የተተከሉ ችግኞችን የመኮትኮት: ዉሃ የማጠጣት እና የመንከባከብ መርሃ ግብር አከናዉነዋል።

የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች በሃገር አቀፍና በከተማ ደረጃ የተያዘዉን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለማሳካት ባለፈዉ ክረምት የተተከሉ ችግኞችን ዉሃ ማጠጣቸዉንና መንከባከባቸዉን አቶ ካሳሁን ተናግረዋል።

ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብም ይገባል ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚዉ በማዕከሉ ከተተከሉት ችግኞች መካከል አብዛኞቹ መጽደቃቸዉንና እንክብካቤ እየተደረገላቸዉ መሆኑን ገልጸዋል።

ሃገሪቱ በአረንጓዴ አሻራ ዘርፍ እያደረገች ያለው እንቅስቃሴ ውጤት ማስመዝገቡን ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የዚህ ሃገራዊ ራዕይ ተሳታፊ በመሆኑ የጀመረዉን ተግባር አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል ::

የጉለሌ ክፍለ ከተማ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ፅህፈት ቤት የእንክብካቤ ዘርፍ ቡድን መሪ አቶ ካሳሁን ግርማ በማዕከሉ ባለፉት ሰባት ዓመታት በርካታ ችግኞች መተካላቸውን አንስተዉ አዲስ ሜዲያ ኔትዎርክ ደግሞ የተከላደው ችግኞች የመንከባከብ እና ውሃ የማጠጣት ተግባር በማከነወን አርአያ በመሆኑ የሚመሰገን ነው ብለዋል ::

የትዉልድ ድምጽ የሆነዉ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ከማድረስ ባለፈ በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮችና የልማት ስራዎች ላይ በመሳተፍ አሻራውን በማስቀመጥ ላይ ይገኛል።

በያለው ጌታነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review