አዲስ አበባ የብልፅግና ተምሳሌት ከተማ

You are currently viewing አዲስ አበባ የብልፅግና ተምሳሌት ከተማ

AMN – ታኀሣሥ 22/2018 ዓ/ም

በአዲስ አበባ ከተማ እየተተገበሩ ያሉ አስደማሚ ልማቶች ከተማዋን የሸፈናት አቧራ ተራግፎ ስሟንና ክብሯን የሚመጥን ውብና ማራኪ አድርጓታል፡፡

ይህ የልማት ሥራ ትውልድ የሚኮራባት ዘመናዊ ገፅታን የሚያጎናጽፍ ሲሆን፤አዲስ አበባ ሰላሟ የተጠበቀ፣ ልማቷ የተሳለጠ፣ እርጅናዋን ቀይራ ስሟንና ታሪኳን በሚገልጽ የለውጥ ጎዳና ላይ የምትገኝ የብዙዎችን ቀልብ የገዛች ምቹ ከተማ መሆን ችላለች።

አሁን አዲስ አበባ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካዊያን መዲና፣ የዓለም የቱሪዝም መስብ፣ የታሪክና የባህል ማዕከል በመሆን የብልጽግና ጉዞዋን በማፋጠን ላይ ትገኛለች።

በመዲናችን በሜጋ ፕሮጀክቶች ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በትምህርት ለትውልድ፣ በኮሪደር ልማትና በበርካታ ሰው ተኮር ተግባራት ነዋሪዎቿን ቀጥተኛ ተጠቃሚ ያደረጉ ሰፋፊ ስራዎች መከናወናቸውን የአደስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ለኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ ገልጿል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review