አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነዉ ተመረጡ

You are currently viewing አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነዉ ተመረጡ

AMN ታኅሣሥ 23/2018

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ማምሻውን ባደረገው ስብሰባ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌን ቀጣዩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ በመምረጥ ውሳኔ አሳልፏል።

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ በአሁኑ ወቅት የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ሆነው በመሥራት ላይ የሚገኙ ሲሆን ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ታዳጊ እና ዋናው ብሔራዊ ቡድንን በአሰልጣኝነት ከመምራታቸው በተጨማሪ ፌዴሬሽኑን በቴክኒክ ዳይሬክተርነት አገልግለዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኙ እየሰሩበት ከሚገኘው ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጋር ንግግር ካደረገ በኋላ የውል ሁኔታ እና ተያያዥ ጉዳዮችን በቀጣይ እንደሚያሳዉቅ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review