ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ምሁራን ሀሳብ አክባሪና አፍቃሪ፣ ጥልቅ አሰላሳይ፣ አንባቢ፣ ችግር ፈቺና መፍትሄ አሳሽ መሆን እንደሚጠበቅባቸዉ ገልጸዋል።
ሀሳብ የለውጥ ኃይል ነው። ምሁራን ደግሞ የለውጥ ወኪሎች ናቸው። ምሁራን በማኀበረሰብ ውስጥ የሚፈጥሩት ለውጥም ሀገርን ወደ ብልጽግና ይወስዳል። በመሆኑም ምሁራን ሀሳብ አክባሪና አፍቃሪ፣ ጥልቅ አሰላሳይ፣ አንባቢ፣ ችግር ፈቺና መፍትሄ አሳሽ መሆን ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ገልጸዋል።
በመድረኩም የኢትዮጵያ ምሁራን በሁለንተናዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ሚና በሚመለከት ሰፊ ውይይት አድርገናል። የመደመር መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሀገራዊ የብልጽግና ጉዞ ላይ አይተኬ ሚና እንዳላቸው በጽኑ ያምናል፣ ለተግባራዊነቱም እየሰራ ይገኛል።
ተቋማቱም የመማር ማስተማር እንዲሁም የምርምር ስራዎችን ከቴክኖሎጂ ጋር በማናበብ ወደ ፈጠራና ተግባር መለወጥ ይጠበቅባቸዋል። ይህም የኢትዮጵያን ብልጽግና በተደመረ አቅም ለማፋጠን ሚናው ከፍተኛ ነዉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት አስተላልፈዋል።