ለ75 ዓመታት ለኢትዮጵያ የእውቀት ብርሃን ያበራው የዕውቀት ቤት – አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ!

You are currently viewing ለ75 ዓመታት ለኢትዮጵያ የእውቀት ብርሃን ያበራው የዕውቀት ቤት – አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ!

AMN — ታኅሣሥ 24/2018 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በትጋት የሚመራ ምርምር፣ በሙግት የሚዳብር ሃልዮት፤ በአመክንዮ የሚበለጽግ ፍልስፍና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መለያ ቀለሞች መሆናቸውን ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ የዕውቀት ብርሃን መፍለቂያ እና የለውጥ ጥሪ ማስተጋቢያ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ ዛሬም የጀመርነውን ልማት በዕውቀት ለመምራት ተደማሪ ጉልበት ነው ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከምሥረታው ጀምሮ የኢትዮጵያ የለውጥ እና የልማት ጥያቄዎች የፈለቁበት፤ የጊዜው ትንታግ ወጣቶች የለውጥ አብዮት የጎሰሙበት የታሪክም የዕወቅትም ቤት ነው።

በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የተደረገው ምክክርም ትናንት እና ዛሬን እንዲሁም ዛሬን እና ነገን፤ ዘላቂ ብልጽግናን ከተሳካ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ጋር አሠናስሎ ለመምራት ጉልበት የሚሰጥ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ተምራችሁ፣ በዕውቀት ተኮትኩታችሁና ካባ ጭናችሁ ዛሬ በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ተቋማት ለምታገለግሉ ምሁራንና ባለሞያዎች እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል።

በተጨማሪም የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያ ለመገንባት በርትታችሁ እየተማራችሁ ላላችሁ ጥበብ ፈላጊ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት በዓል አደረሳችሁ በማለት የመልካም ምኞት መልዕክትም አስተላልፈዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review