የትግራይ ክልል ችግር በምክክር እንደሚፈታ እናምናለን ሲሉ በትግራይ ክልል የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ

You are currently viewing የትግራይ ክልል ችግር በምክክር እንደሚፈታ እናምናለን ሲሉ በትግራይ ክልል የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ

AMN ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያይቷል፡፡

ውይይቱን የከፈቱት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽር መስፍን አርዓያ (ፕሮፌሰር) ኮሚሽኑ ባለፉት ጊዜያት ያከናወናቸውን ተግባራት ለተሳታፊዎቹ አብራርተዋል፡፡

ያለ ትግራይ ክልል ተሳትፎ ምክክሩን መቋጨት ስለማይታሰብ፣ ትግራይ ክልልን በምክክር ሂደቱ ለማሳተፍ በኮሚሽኑ በኩል በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ አንስተዋል፡፡

በመሆኑም በክልሉና በመላ ሀገሪቱ የሚሳተፉ የትግራይ ክልል ፖለቲካ ፓርቲዎች ይህ ሂደት እንዲሳካ ከኮሚሽ ጎን ሆነው ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

በውይቱ የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል ምክክር እንዲካሄድ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አድንቀዋል፡፡

የትግራይ ክልል ችግር በውይይት እንደሚፈታ እምነታቸው መሆኑን የገለፁት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮቹ ለዚህም ሀገራዊ ምክክሩ ብቸኛ አማራጭ መሆኑን አስምረውበታል፡፡

እንደ ተሳታፊዎቹ አስተያየት የትግራይ ክልል የምክክሩ አካል መሆን አለበት፤ ኮሚሽኑ የጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ በመቀጠል ምክክሩን መጀመር አለበት፡፡

በውይይቱ የአረና፣ ባይቶና ፣ የወለዶ ትግራይ፣ የቃንጫ ሃቂ፣ የትግራይ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ትዴፓ)፣ የትንሳኤ እንደርታ እና የራያ ራዩማ ፓርቲ አመራሮች ማሳተፋቸዉን ኮሚሽኑ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review