ማንችስተር ዩንይትድ በጊዜያዊ አሰልጣኝ ዳረን ፍሌቸር እየተመራ ከበርንሌ ይጫወታል

You are currently viewing ማንችስተር ዩንይትድ በጊዜያዊ አሰልጣኝ ዳረን ፍሌቸር እየተመራ ከበርንሌ ይጫወታል

AMN ታኅሣሥ 29 ቀን 2018 ዓ.ም

አሰልጣኙ ሩበን አሞሪም እና ረዳቶቹን ያሰናበተው ማንችስተር ዩናይትድ በጊዜያዊ አሰልጣኝ ዳረን ፍሌቸር እየተመራ በርንሌይን ይገጥማል፡፡

በበርንሌይ ሜዳ ተርፍ ሙር በሚከናወነው ጨዋታ ዩናይትድ በፍሬቸልር ስር ምን እንደሚመስል ለማየት በርካታ ደጋፊዎች ጓጉተዋል፡፡

ምሽት 5፡15 በሚጀምረው ጨዋታ በዩናይትድ በኩል ቡርኖ ፈርናንዴዝ እና ሜሰን ማውንት ወደ ስብስቡ እንደሚመለሱ ዳረን ፍሌቸር አረጋግጧል፡፡

ከሩበን አሞሪም ጋር ጥሩ ግንኙነት ያልነበረው ኮቢ ማይኑም ወደ ልምምድ ተመልሷል፡፡ የስብስቡ አካል መሆን አለመሆኑ ግን አልታወቀም፡፡

ማንችስተር ዩናይትድን መምራት ትልቅ ክብር እንደሆነ የገለፀው ዳረን ፍሌቸር በምሽቱ ጨዋታ ሦስት ነጥቡን ማሳካት ወሳኝ እንደሆነ ተናግሯል፡፡

አሰልጣኙ ከአጨዋወት ጋር በተያያዘ ጥያቄ ተነስቶለት በሦስት ይሁን በአራት ተከላካይ አሁን ላይ መግለፅ አልችልም ሲል አልፎታል፡፡ ፍሌቸር ከ18 ዓመት በታች ቡድኑን ሲመራ 4 -3 -3 የሚጠቀመው የጨዋታ አሰላለፍ ነው ፤ በዛሬው ጨዋታም ተመሳሳዩን ይጠቀማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በ11 ተከታታይ የሊግ ጨዋታ አንድም ማሸነፍ ያልቻለው በርንሌይ በዛሬውም ጨዋታ ድል የማድረግ እድሉ ጠባብ ይመስላል፡፡ ማንችስተር ዩናይትድ በተርፍ ሙር ባስተናገደበት ዘጠኝ ጨዋታ አንድ ብቻ ነው ያሸነፈው፡፡

ሁለቱ ክለቦች በኦልድትራፎርድ ያደረጉት የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ በዩናይትድ 3ለ2 አሸናፊነት መተናቀቁ ይታወሳል፡፡

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review