አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በኪነ ጥበብ ዘርፉ ሙያና ሙያተኛውን በማገናኘትና ኪነ ጥበብን በማሳደግ የትውልድ ድምፅ ሆኖ በማገልገል ላይ እንደሚገኝ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገለጹ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በኪነ ጥበብ ዘርፉ ሙያና ሙያተኛውን በማገናኘትና ኪነ ጥበብን በማሳደግ የትውልድ ድምፅ ሆኖ በማገልገል ላይ እንደሚገኝ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገለጹ

AMN-ታኅሣስ 29/2018

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በኪነ ጥበብ ዘርፉ ሙያና ሙያተኛውን በማገናኘትና ኪነ ጥበብን በማሳደግ የትውልድ ድምፅ ሆኖ በመስራት ላይ እንደሚገኝ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገለጹ::

ለአንድ ዓመት የዘለቀው የአዲስ ታለንት ሾው የፍጻሜ ዉድድር የአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) ና የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋን ጨምሮ ሌሎች የከተማዉ ከፍተኛ አመራሮች፤ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የቦርድ አባላትና የማኔጅመንት አባላት፤ የሁሉም ክፍለ ከተሞች አመራሮች፤ ዳኞች፤ ተወዳዳሪዎች፤ የኤኤምኤን ሌሎች አመራሮችና ሰራተኞችና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች በተገኙበት በአድዋ ድል መታሰቢያ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኤኤምኤን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ፣የትውልድ ድምፅ የሆነዉ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከተሰጠዉ ተልእኮ አንጻር ከተማዊ፣ሀገራዊና ዓለማቀፍዊ ይዘቶችን በፍጥነትና በጥራት ተደራሽ በማድረግ የተጣለበትን ሃላፊነት በመወጣት ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል።

አዲስ አበባ ከዕለት ወደ ዕለት አስደማሚ ለውጦችን እያስመዘገበች መምጣቷን ያነሱት ዋና ስራ አሰፈፃሚው፣ ከተማዋ ያላትን የቱሪዝም መዳረሻ ከማስተዋወቅና የኪነ ጥበብ ዘርፉን በማሳደግ ሰፊ ስራዎችን መስራቱን አንስተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት የመክፈቻ ስነ ስርዓቱ የተከናወነውና ዛሬ ፍፃሜውን የሚያገኘው አዲስ ታለንት ሾው በዘርፉ ከተሰሩት ስራዎች ቀዳሚ ማሳያ ነዉ ብለዋል።

ዉድድሩ መዘጋጀቱ ከማዝናናት ባለፈ የመዲናዋ ወጣቶች , በሚፈልጉት የጥበብ ዘርፍ ራሳቸዉን ፈልገዉ እንዲያገኙ ትልቅ እድል መፍጠሩን ገልጸዋል፡፡

ኤኤምኤን በኪነ ጥበብ ዘርፉ ሙያና ሙያተኛውን በማገናኘት የትውልድ ድምፅ ለመሆን ያስቀመጠውን ራዕይ በተግባር ያረጋገጠበትም እንደሆነ አቶ ካሳሁን አንስተዋል።

ተቋሙ ተመራጭና ተደራሽ ለማድረግ የተጀመረው የሪፎርም ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያነሱት ዋና ስራ አስፈጻሚዉ ኤኤምኤን በይዘት አቀራረብና በቴክኖሎጂ ለውጥ ለማምጣት ለሚያደርገዉ ጥረት የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በልዩነት የመጣው “አዲስ ታለንት” ሾው በሰባት ምዕራፎች ሲካሄድ ቆይቷል።

ከፍተኛ ሽልማት በተዘጋጀበት በዚህ ውድድር ላይ በሦስት ዘርፎች በሙዚቃ ፣ በሰርከስ እና በትወና ዘርፎች የአሸናፊዎች አሸናፊ ይወዳደራሉ፡፡

በሚካኤል ሂሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review