በኢትዮጵያ በመከናወን ላይ በሚገኙ የመኖሪያ ቤት ልማት ሥራዎች ለችግር ተጋላጭ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ አባወራዎችና እማወራዎች አስተማማኝ መጠለያ ማግኘት ችለዋል

You are currently viewing በኢትዮጵያ በመከናወን ላይ በሚገኙ የመኖሪያ ቤት ልማት ሥራዎች ለችግር ተጋላጭ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ አባወራዎችና እማወራዎች አስተማማኝ መጠለያ ማግኘት ችለዋል

AMN ጥር 13/2018

በኢትዮጵያ በመከናወን ላይ በሚገኙ የመኖሪያ ቤት ልማት ሥራዎች በሺዎች የሚቆጠሩ እና ለችግሩ ተጋላጭ የሆኑ አባወራዎችና እማወራዎች አስተማማኝ መጠለያ ማግኘት ችለዋል።

በቤተሰብ ደረጃ ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ዘላቂ እና አስተማማኝ መኖሪያዎችን በማስፋት የኑሮ ሁኔታን በማሻሻል ላይ ይገኛሉ።

ምንም እንኳን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት አሁንም ከፍተኛ ቢሆንም፥ የኢትዮጵያ መንግሥት መደበኛ የቤት አቅርቦትን ከማህበራዊ ድጋፍ ጋር በማቀናጀት ሰፊ ስራዎችን እየከወነ ይገኛል።

ቀጣይነት ካላቸው የከተማ እና የህብረተሰብ ተኮር የቤት ልማት መርሃ ግብሮች በተጨማሪ፤ ዓመታዊው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የመንግሥት ዋነኛ መርሃ ግብር ሆኖ ቀጥሏል።

ይህ መርሃ ግብር በጎ ፈቃደኞችን እና የመንግሥት ተቋማትን በማስተባበር በፈራረሱ ቤቶች ውስጥ ወይም ለጎርፍ አደጋ በሚጋለጡ አካባቢዎች የሚኖሩ አረጋውያንን እና የአቅመ ደካማ ዜጎችን ቤቶች የመጠገንና የመገንባት ስራ ያከናውናል።

በእነዚህ የተቀናጁ ጥረቶች አማካኝነት በሺዎች የሚቆጠሩ እና ለችግሩ ተጋላጭ የሆኑ አባወራዎችና እማወራዎች አስተማማኝ መጠለያ ማግኘት የቻሉ ሲሆን፤ ይህም እንደ ሀገር አካታች ልማትን ለማረጋገጥና የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል ኢትዮጵያ እውን እያደረገች ያለውን የማያቋርጥ እድገት የሚያሳይ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review