በሰው ኃይል፤ በትጥቅ እና በውጊያ መሠረተ-ልማት ግንባታ ከፍተኛ ሥራ ተሠርቷል – ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ

You are currently viewing በሰው ኃይል፤ በትጥቅ እና በውጊያ መሠረተ-ልማት ግንባታ ከፍተኛ ሥራ ተሠርቷል – ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ

AMN ጥር 19 / 2018 ዓ.ም

90ኛ ዓመት የኢትዮጵያ አየር ኃይል የምሥረታ በዓልን ተከትሎ የአየር ኃይል አካዳሚ በተለያየ የሙያ ዘርፍ ያሠለጠናቸውን አብራሪዎችና ሙያተኞችን በዛሬው ዕለት አሥመርቋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የአየር ኃይል አካዳሚ ተማሪዎች የምረቃ በዓል ላይ ተገኝተው ብልጫ ላስመዘገቡ የመጀመሪያ ደረጃ በረራ ተማሪዎች የትክሻ ምልክት በማልበስ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ከተቋሙ የተሰጠንን ተልዕኮ መነሻ በማድረግ ባለፉት 8 ዓመታት በሰው ኃይል ግንባታ፣ በትጥቅ እና በውጊያ መሠረተ-ልማት ግንባታ ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ የመፈፀም አቅማችንን ወደ ላቀ ደረጃ እያሸጋግረን እንገኛለን ብለዋል።

ቀደምትነትን ያረጋገጠ ኃይል ፈጥኖ ድል የሚቀዳጅ መሆኑን በመረዳት የኢትዮጵያ አየር ኃይልም ከዘመኑ ጋር በመዘመን ወቅታዊ ተለዋዋጭ አለማዊ ሁኔታን ተረድቶ ውጊያን በላቀ ጀግንነት መፈፀም የሚችል የኢትዮጵያን የአየር ክልል የሚያስጠብቅና የአየር የበላይነትን የሚያረጋግጥ አንጋፋ ተቋም ሆኖ እየተገነባ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

የምረቃ ስነ-ስርዓት ልዩ የሚያደርገው ከበርካታ አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት ሴት አብራሪዎች የበረራ ስልጠናቸውን በከፍተኛ ውጤት በማጠናቀቅ ሴቶች ከወንዶች እኩል ማንኛውንም ፈታኝ ሁኔታዎች ተቋቁመው የላቀ ድል ማስመዝገብ የሚችሉ መሆናቸውን ያሥመሰከሩበት መሆኑ ነው ብለዋል።

ተመራቂዎች በስልጠና የፈጠሩትን አቅም በመጠቀም ለተቋሙ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረከቱ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ማሳሰባቸዉን የሃገር መከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review