AMN ጥር 26 / 2018
በገጠርና ከተማ አኗኗርን ለማሻሻል የተሰራው ስራ የሚታይ ለውጥ የተገኘበት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በኮሪደር ልማት ብዙዎችን ያስገረመ መሻሻልና እድገት የታየበት መሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ይህን ያሉት የመንግሥትን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም በሚመለከት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ነው፡፡
ከውጪ የሚመጡ በርካታ ሰዎች ሰዎች አዲስ አበባ እንደዚህ ውብ ከተማ መሆኗን አልገመትኩም በማለት በለውጡ እንደሚገረሙ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ በኢትዮጵያ የተሰሩት ስራዎች እመረታዊ ለውጥ ያመጡ ናቸው ብለዋል፡፡
አቅሙ ያላቸው ሰዎች ወጣ ብለው ከሌሎች ጋር ቢያጻጽሩት ፣ ብዙ ሀገራት ከዚህ ቀደም በነበሩበት ወይም ባነሰ ሁኔታ ነው ውስጥ መሆናቸውን ይረዳሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስሩ ፣ የሚታይ ለውጥ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ብለዋል፡፡

በገጠር ኮሪደር በእያንዳንዱ ወረዳ ቢያንስ አንድ አንድ መንደር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
እያንዳንዱ የአርሶ አደር ቤት ሶላር ያለው ፣ ባዮ ጋዝ ያለው ፣ ከብት እና ሰው ተለያይቶ የሚኖርበት አውድ እየተፈጠረ መሆኑን ጠቅሰው ይህም የአኗኗርና የጤና መሻሻል የሚያመጣ መሆኑን አብራተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ፣ ለጤና ከመመደብ በሽታው እንዳይመጣ መስራት በጣም ስለማያግዝ አኗኗርን ማሻሻል ላይ አተኩረናል ብለዋል፡፡
የአረንጓዴ ልማት ስራዎች የወንዝ ዳርቻዎች ልማት ፣ የመንገድ ዳር መራመጃዎች የመሳሰሉት ስራዎችም ከጤና አጠባበቅ ጋርም የተሸለ ለውጥ ማምጣት የሚያስችሉ መሆናቸውን ነው የጠቀሱት፡፡
የክረምት በጎ ፈቃድ ፣ በመንግስትና ግሉ ሴክተር አጋርነት የሚገነቡ ቤቶች ሲደማመሩር ጥሩ እንቅስቃሴ እንዳለም አብራርተዋል፡፡
ታደሰ ሽፈራው