የዓለም ባንክ የኦፕሬሽን ፖሊሲና የሃገራት አገልግሎት ተጨባጭ ለውጥ በሚያመጡ ስራዎች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን ገለጸ

You are currently viewing የዓለም ባንክ የኦፕሬሽን ፖሊሲና የሃገራት አገልግሎት ተጨባጭ ለውጥ በሚያመጡ ስራዎች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን ገለጸ

AMN ጥር 26/ 2018 ዓ.ም

የዓለም ባንክ የኦፕሬሽን ፖሊሲና የሃገራት አገልግሎት ተጨባጭ ለውጥ በሚያመጡ ስራዎች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን የባንኩ ምክትል ፕሬዝዳንት ጋሊና ቪንሴሌት ገለጹ።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ፣ ከዓለም ባንክ የኦፕሬሽን ፖሊሲና አገራት አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ጋሊና ቪንሴሌት ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በዋናነት ስትራቴጂካዊ አጋርነትን ይበልጥ ለማጠናከር በሚያስችለው አዲስ የአገራት አጋርነት ማዕቀፍ ላይ ያተኮረ ነበር።

ወደፊት የሚደረጉ ትብብሮች ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የልማትና የሪፎርም ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ ማስቻል በሚቻልበት ሁኔታ እና በአዲሱ የዓለም ባንክ የአገራት ተሳትፎ ማዕቀፍ ዙሪያ ሰፊ ምክክር አድርገዋል።

ሚኒስትሩ ዓለም ባንክ በቅርቡ ተግባራዊ ያደረገውን እና ውጤት ተኮር በሆኑ ተግባራት ላይ ትኩረት የሚያደርገውን አዲስ የአገራት ተሳትፎ አካሄድ አድንቀዋል።

ይህ አዲስ አቀራረብ ከባንኩ ጋር ያለውን አጋርነት ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ መልካም አጋጣሚ መሆኑንም ገልጸዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንት ጋሊና ቪንሴሌት በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ መንግስት እያከናወነ ያለውን የሪፎርም ስራ እና ጠንካራ የኢኮኖሚ አመራር አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ባንኩ ተጨባጭ ለውጥ በሚያመጡ ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆኑንም በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ሁለቱም ወገኖች አዲሱን የሃገራት አጋርነት ማዕቀፍ ለማዘጋጀት በጋራ እና በትብብር ለመስራት መስማማታቸዉን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review