AMN ጥር 27/ ቀን 2018 ዓ.ም
አርሰናል ቼልሲን በደርሶ መልስ በማሸነፍ የካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል።
በኤምሬትስ የተደረገውን የመልስ ጨዋታ ባለሜዳው 1ለ0 አሸንፏል። ብቸኛውን ግብም ተቀይሮ የገባው ካይ ሀቨርትዝ 97ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
በስታምፎርድ ብሪጅ የተከናወነውን የመጀመሪያውንም ጨዋታ 3ለ2 ያሸነፈው አርሰናል በድምር ውጤት 4ለ2 በማሸነፍ የፍፃሜ ተፋላሚ ሆኗል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ በካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ሲደርስ ከስምንት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ሚካኤል አርቴታ አርሰናል ከተረከበ በኋላ ለፍፃሜ ጨዋታ ሲበቃ ሁለተኛው ነው።
ስፔናዊው አሰልጣኝ በ2020 የኤፍ ኤ ካፕ ፍፃሜ ደርሶ ቼልሲን 2ለ1 በመርታት ዋንጫ ማንሳቱ ይታወሳል።
አርሰናል በካራባኦ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ የማንችስተር ሲቲ እና ኒውካስትል ዩናይትድ አሸናፊን ይገጥማል።
በሸዋንግዛው ግርማ