AMN – የካቲት 10/2017 ዓ.ም
38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 46ተኛው የአፍሪካ ኀብረት መደበኛ የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ በስኬት መጠናቀቁን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
መግለጫውን የሰጡት የአገልግሎቱ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ፤ ኢትዮጵያ ከጉባዔው በዋናነት ሶስት ስኬቶችን አስመዝግባለች ብለዋል።
ኢትዮጵያ በተለይም ደግሞ አዲስ አበባ በተቋማት ትብብር የተመራ አለም እና አህጉር አቀፍ ብሎም ሀገራዊ ዝግጅቶችን በብቃት ማዘጋጀት እንደሚቻል ያረጋገጠችበት ጉባዔ መሆኑን ገልፀዋል።
ሌላው ደግሞ የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ በማስተዋወቅና በመገንባት ያለችበትን ፈጣን እድገት ለሌሎች ሀገራት ያሳየችበት ነው ብለዋል።
ከዚህ ባሻገር ከመሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን በማካሄድ ወሳኝ የዲኘሎማሲ ስራዎች መሰራታቸውን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
አዲስ ኮንቬንሽን ማዕከልን አለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በማስገንባቱና ለተለያዩ ስብሰባዎች አገልግሎት እንዲሰጥ ማስመረቁ መልካም ተግባር መሆኑን የአገልግሎቱ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ገልፀዋል።
በንጉሱ በቃሉ