አይሾው ስፒድ በአዲስ አበባ የታዘባቸው አስገራሚ እውነታዎች እና የኢትዮጵያ ቡና ጉልበት

You are currently viewing አይሾው ስፒድ በአዲስ አበባ የታዘባቸው አስገራሚ እውነታዎች እና የኢትዮጵያ ቡና ጉልበት

AMN- የካቲት 16/2018 ዓ.ም

ዓለም አቀፍ ዝናን ያተረፈው ዝነኛው ዩቲዩበሩ አይሾው ስፒድ (IShowSpeed) በኢትዮጵያ በነበረው ቆይታ፣ በአዲስ አበባ ዘመናዊነት፣ በኢትዮጵያ ልዩ የዘመን አቆጣጠር እና በታሪካዊ ጥንካሬዋ መገረሙን ለሚሊዮን ተከታዮቹ አጋርቷል።

በተለይ የኢትዮጵያ ቡና ያሳደረበት “ኃይል” እና የፈጠረበት ድንገተኛ ስሜት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ መነጋገሪያ ሆኗል።

ዓለም አቀፍ ዝናን ያተረፈው ዩቲዩበሩ አይሾው ስፒድ (IShowSpeed) በኢትዮጵያ ቆይታው በታዘባቸው ነገሮች በጣም መገረሙን ለተከታዮቹ አጋርቷል።

ስፒድ በተለይ የአዲስ አበባን ዘመናዊ ገጽታ ሲመለከት፤ የሥነ-ህንፃ ጥበባቸው እጅግ ዘመናዊና አፍሪካዊ ውበትን ያዋሃደ ነው፤ በጉዞዬ ካየኋቸው ሁሉ ምርጡን መሰረተ ልማት እዚህ አግኝቻለሁ” ሲል አድናቆቱን ችሯል።

የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠርም ሌላው የግርምት ምንጭ ሆኖታል። እርሱ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ላይ ሆኖ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር 2018 መሆኑን ሲያውቅ እጅግ መገረሙን ተናግሯል።

“ወደ ኋላ በጊዜ የተጓዝኩ ያህል ነው የተሰማኝ፤ እንደ ህጻን ልጅ ደስ ብሎኛል” በማለት ስሜቱን ገልጿል። ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ያልተገዛች ሀገር መሆኗም “እጅግ አስገራሚ እውነታ”ሲል ተደሟል።

ለወትሮው ቡና የማይጠጣው ስፒድ፣ በቡና መገኛዋ ኢትዮጵያ ግን ሳይቀምስ አላለፈም። የኢትዮጵያ ቡና “ኃይል” ግን አልቀለደበትም።

ቡናውን እንደጠጣ በቀጥታ ስርጭቱ ላይ ሲጮህ፣ ሲገለባበጥና ከኢትዮጵያውያን ጋር ሲጨፍር አምሽቶ፣ በመጨረሻም ጉልበቱ አልቆ “በታሪኬ ለመጀመሪያ ጊዜ ራሴን ስቼ ወደቅሁ” ሲል የቡናውን አነቃቂነት መስክሯል።

ከቁጥጥር ውጪ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ያሳለፈው ጊዜ ግን እጅግ ደማቅና የማይረሳ እንደነበር ስፒድ አረጋግጧል።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review