ለሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ስኬት ከአዲስ አበባ ከተማ የተገኘው ልምድና ተሞክሮ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አበርክቷል

You are currently viewing ለሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ስኬት ከአዲስ አበባ ከተማ የተገኘው ልምድና ተሞክሮ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አበርክቷል

AMN- የካቲት 17/2018 ዓ.ም

ለሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ስኬት ከአዲስ አበባ ከተማ የተገኘው ልምድና ተሞክሮ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ማበርከቱን የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ገልፀዋል።

አዲስ አበባን መነሻ አድርጎ በበርካታ የኢትዮጵያ ከተሞችና ገጠሮችም ጭምር የተስፋፋው የኮሪደር ልማት፣ ተወዳዳሪና ለኑሮ ምቹ ከተሞችን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው።

የኮሪደር ልማቱ ተጨማሪ ድምቀትና ውበት ካጎናፀፋቸው ከተሞች አንዷ የሆነችው የሀዋሳ ከተማ፣ የሁለተኛ ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ስራዋን እያጠናከረች ትገኛልች፡፡

አዲስ አበባ የመጀመሪያው የኮሪደር ስራ እንደመሆኑ ብዙ ልምድ እንዳልነበረንና፣ በተለይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቀጥተኛ ድጋፍ የነበረበት በመሆኑ ብዙ ትምህርት የተገኘበት፣ ብዙ አቅም የተገነባበት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከንቲባው ከአዲስ አበባ ከተማ ኮሪደር ልማት ልምድ በመውሰድ ሃሳብም ጭምር በተሟላ መንገድ ተገንዝቦ ወደ ስራ ወደ መሬት ከማውረድ አንፃር የነበሩትን ጉድለቶች በመሙላት አቅም እንድንገነባ አድርጎናል ብለዋል።

ያንን ልምድና ተሞክሮ ወደ ሀዋሳ በመውሰድም በከፍተኛ ሁኔታ እንደጠቀማችው ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደ ሀገር የከተሞችን ልማት ለማፋጠንና የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ ለመቀየር ይሄን ሃሳብ ካስጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ፣ በተለይ በአዲስ አበባ ሰፊ ስራዎች ትልቅ ውጤት መጥቶ ዛሬ በሁሉም የሀገራችን ከተሞች የኮሪደር ልማት ስራ መስፋፋት ችሏል።

በከተማዋ በኮሪደር ልማት ሥራው 2 ሺህ 265 የሚደርስ ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ እድል መፈጠሩንም ከንቲባው አስታውቀዋል።

በቶለሳ መብራቴ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review