AMN የካቲት 18 / 2018 ዓ.ም
የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) እና ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ፕሬዝዳንቱ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለቱን አገራት ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግሥት ከፍተኛ መሪዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡